Saturday, July 30, 2016

ወያኔዎች ስልጣንን ነክሶ፣ “አንገታችን እስክቆረጥ ድረስ በምርጫም ይሁን በምን ስልጣንን አንለቅም፣ በደም ያመጣነውን በደም እንሰጣለን” የሚሉበት ዋና ምክንያት ያውቃሉ?

ወያኔዎቹ ኢትዮጵያኖችን እየጭፈጨፉና እያሰሩ የቀጠሉበት እንድሁም ስልጣንን ነክሶ፣ “አንገታችን እስክቆረጥ ድረስ በምርጫም ይሁን በምን  ስልጣንን አንለቅም፣ በደም ያመጣነውን በደም እንሰጣለን” የሚሉበት ዋና ምክንያት፣ በምድር ላይ ከተፈጠሩበት ጊዜ አንስቶ አይቶ የማያውቁት ሀብት ሲለዘረፉና ንብረት ሲላፈሩ ስልጣንን ከለቀቁ ወደ ጣኔና ወደ ድንጋያቸው እንዳይመልሱ ፈርተውት ነው። ወያኔዎቹ  በዚህ ሁኔታ ከቀጠሉ ወልቃይትን ከአማራ በግድ ለውስድ እንዳወጁ ሁሉ፣ በአዲስ አባባ (ፊንፊኔ) ውስጥ ትግሬን እያሰፈሩ ነባር የአዲስ አበባን ንብረት ወደ ትግሬ ንብረት እየቀየሩ ሲልሆኑ፣ በብዛትም ቀይሮ ሲለተሳካላቸው አዲስ አበባን በወረቀት የኦሞሮ ላይ የኦሮሞ ናት እያሉ፣ በተጨባጭ ግን አዲስ አበባን በትግሬና በትግሬ ንብረት እየሞሉ ይገኛሉ። አዲስ አበባ (ፊንፊኔ) የትግሬ እንድትሆን ጉልህ ሚና የተጫወቱት በኦሮሞ ስም ወያኔዎቹ ለራቸው ጥቅም የጠፈጠፉት የኦህዴድ (የOPDO) ባለስልጣኖች ናቸዉ።

 ወያኔ በጨበጠው ስልጣንና ጠበንጃ ተጠቅሞ ከኢትዮጵያኖቹ በተለይ ኦሮሞቹን የሚጨፈጭፍበት፣ የሚያስርበት፣ ከሀገር የሚያሳድድበት,  እንድሁም የኦሮሞ የፖሊቲካ ፓርቲዎች እንዳይጠናከሩ ብዙ ሚሊዮን  ዶላር ባማፍሰስ ሸሪ የሚሸሪብበት ዋና ምክንያት ከኦሮሚያ የዘረፈውን ሲለምያውቅና ኦሮሞ ከተጠናከረ ወያኔ እሳት ውስጥ እንደገባ  ቅቤ እንድቀልጥ ስሚያውቅ ነው።  የአለም ፖሊቲካ ሁኔታው በለስ የቀናው ወያኔ፣ በተለይ በምስራቅ አፍርካ የአሜሪካ ተላላኪ ሲለሆነ፣ እኛ በወያኔ ብንጨፈጨፍም ለፈረንጆች ጉዳያቸው አይደለም።  ፈረንጅ ጠበንጃና ሀይል ያለው ጎን በመሰለፍ የራሱን ጉዳይ ሲለሚያስፈጽም  ከወያኔ በላይ ጠንካራ ሃይል መፍጠር አለብን።

በኢትዮጵያ ታርክ እንደ ወያኔ ዘረኛ መንግስት በኢትዮጵያ ምድር ተፍጥሮ አይታወቅም። በንጉሱ ጊዜያት ነፍጠኞችና ፍውዳሎች አማራ ብቻ አልነበሩም፣ ከኦሮሞችና ከሌሎች ብሔሮች ነፍጠኞችና ፈውዳሎች ነበሩ። ዛሬ ግን የኢትዮጵያ ስልጣንንና ሀብት በሙሉ የተቆጣጠሩት ፍውዳሎችና ነፍጠኞች ትግሬዎች (ወያኔዎች)  ብቻ ናቸው። በደርግ ጊዜም ቢሆን ደግሞ ስልጣንና ሀብት እንደ ዛሬ በአንድ ብሔር እጅ  አልነበረም።

ኢትዮጵያኖችን  በረሃብና በጠነ እየቆሉ ወያኔዎቹ የኢትዮጵያውንን ሀብት ወደ ዉጪ ሀገር በማሸሽና ለፈረንጅ የስራ እድል እየፈጠሩለት ይገኛሉ። በቅርቡ 15 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ሲራቡ  ፈረንጅና ዲያስፖራ ከኢትዮጵያ የሚመጣውን እንጄራ በፈልጉበት ጊዜ ይበላሉ። የኢትዮጵያ የጤፍ እንጄራና ዱቄትም በአውሮፓና በአሜሪካ ከሀብሻ ሬስቶራንቶችና ሱቆች አልፎ ተርፎ በፈረንጆች ሱፐርማርኬቶች ውስጥ እየተሸጠ ይገኛል።  ጤፍ በዶላር ወደ ውጪ ሀገረ ሲለሚትሸጥ የጤፍ ዋጋ መናሪን በተመልከተ የቀድሞ ጠ/ም መለስ ዜናዊ፣ “የጤፍ ዋጋ የመናሩን ጉዳይ ጤፍ የማይበሉ ኢትዮጵያውያን ጤፍ መብላት ስለጀመሩ ነው” ብሎ  ለይስሙላ ፓርላማች ተናግረዋል።  የአሁኑ የይስሙላ ጠ/ም ኋ/ማሪያም ደሳለኝም የአባቱን የመለስ ዜናዊ አባባል ለአሻንጉልት ፓርላማቸው በመድገም ተናግሯል።           


No comments:

Post a Comment